Up next


ቢዝነስ ለመጀመር ጠቃሚ መረጃ [ሰሞኑን] [semonun]

58 Views
መዝናኛ
7
Published on 17 Jul 2019 / In Shows

የራሳችሁን ቢዝነስ ለመጀመር የምታስቡ ከሆነ ይሄን መስማት የግድ ነዉ! ብዙ ሰዎች አሁን ካላቸዉ ኑሮ የተሻለ ህይወት ለመኖር ይመኛሉ፡፡ ምኞት ብቻዉን ግን በቂ አይደለም፡፡ ብዙዉን ጊዜ ምኞት በስራና በጠንካራ ዲሲፕሊን ካልታገዘ የሚያልሙትን ህይወት ማግኘት ከህልምነት አያልፍም፡፡ በምኞት ብቻ የሚዋልሉ ሰዎች አቋራጭ ፍለጋ ላይ ያተኩራሉ፡ ሎተሪ መቁረጥ፣ ሃብታም ባል ወይንም ሚስት ፍለጋ መባዘን፣ ስራ ላይ በሚከሰት አደጋ ጠቀም ያለ ካሳ ለማግኘት ማለም፣ ዉርስ መጠበቅ፣ ሙስና፣ ወዘተ፡፡ ምንም እንኳን ከላይ የተጠቀሱት እና ሌሎች አቋራጮች አልፎ አልፎ ቢሳኩም አብዛኛዉን ጊዜ ግን መና ሆነዉ ሲቀሩ ይታያል፡፡
ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ደግሞ በተቃራኒዉ ገና በጠዋቱ እጅ ሰጥተዉ ያለ ህልም ወይንም ራእይ እድሜያቸዉን ይገፋሉ፡፡ በህሊናቸዉ ነገሮች ከባድ እንደሆኑ እና የተሳካ ህይወት የነርሱ ሊሆን እንደማይችል ራሳቸዉን አሳምነዉ ተቀምጠዋል፡፡ እኔማ ተምሬ ዲግሪ አልይዝም፣ የራሴን ቤት ሰርቼ ከኪራይ ልወጣ የማይታሰብ ነዉ፣ክብደትማ በፍፁም መቀነስ አልችልም፣ ወዘተ እንደዚህ አይነት አስተሳሰቦች ብዙዎችን ሳይሞክሩ እጅ እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል፡፡
በጣም በርካታ ሰዎች እድሜያቸዉን ሙሉ ለዚህ ወይንም ለዚያ ድርጅት ሲሰሩ አሳልፈዉ የጡረታ ጊዜ ሲቃረብ እንዴት እሆን ይሆን የሚለዉ ስጋት መምጣት ይጀምራል፡፡ እድሜ እየገፋ ሲሄድ አቅም ስለሚቀንስ ተሯሩጦ መስራት አማራጭ አይሆንም፡፡ ለጤና የሚደረገዉ ወጪም እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የጡረታዉ ገቢም የሚያወላዳ አይደለም (በተለይም የዋጋ ግሽበት በቀጣይነት ሊኖር ስለሚችል) ፡፡ በደህና ጊዜ ልጆቹን ለቁምነገር ያበቃ የልጆቹን እጅ ማየት ሊኖርበት ነዉ፡፡ አሊያም ልጆቹን ያሳደገበትን ቤት ሸጦ ትንሽ ቤት ሰርቶ ወይ ገዝቶ ቀሪዉን እየበላ ኑሮዉን ይገፋል፡፡

ይህን እንደመንደርደሪያ ካልን የናንተም ጥይቄ ይሆናል ብለን የምንጠብቀዉ ታዲያ ሃብታም መሆን እንዴት ይቻላል? የሚል ነው!
በዛሬው ቪዲዮ የተወሰኑትን እናያለን። ቀጣይ ቪድዮዎችንም በቀላሉ ማግኘት እንድትችሉ ሰብስክራይብ በማድረግ የሰሞኑን ዩቲዩብ ቻናል ደንበኛ እንድትሆኑ እንጋብዛለን!
visit our website at www.semonun.com
የፌስቡክ ፔጃችን ደምበኛ ይሁኑ፡ www.facebook.com/semonun

አዲስ ቢዝነስ ለመጀመር፣ ገንዘብ የማግኛ መንገድ፣ ሃብታም ለመሆን፣ ገንዘብ እንዴት ማግኘት ይቻላል፣ ቢዝነስ ለመጀመር

Show more
Facebook Comments

Up next