Up next


ነብይ ኢዩ ጩፋ ለዶ/ር አብይ አህመድ የፃፈው አነጋጋሪ ደብዳቤ

89 Views
Ethio News
6
Published on 14 Jul 2019 / In Religious

አስቸኳይ መልዕክት ለዶ/ር አብይ አህመድ

ስለ ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ ከመናገሬ በፊት ኢትዮጵያ የሚለው ቃል እንደ ድልድይ ተጠቅሜ ወደ ሚቀጥለው ሀሳብ ብገባ መልካም እንደሆነ ተሰማኝ ስለ ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ እያልክ ስለ ኢትዮጵያ ለምን ታነሳለ የሚሉ አንዳንድ የዋሃ ሰዎች ስለማይጠፋ ማለት ነው፡-
 ርዕሱ ዶ/ር አብይ ሆኖ ኢትዮጵያን መንካት የቻልኩት ዋናው ጉዳይ ኢትዮጵያን ከዶ/ር አብይ ዶ/ር አብይን ከኢትዮጵያ ነጥሎ ማውራት የማይቻል ሀቅ ስለሆነ ኢትዮጵያ ብዬ መጀመር ግድ ሆነብኝ፤ ገና ወደ ቤተ-መንግስት ፊቱን እንዳቀና ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል በመናገር አለምን ጉድ ማስባሉ የማይረሳ ትዕይንት ነው፡፡
 ኢትዮጵያ የምትባል አገር ወፍ ዘራሽ እግረ መንገድ የተፈጠረች ምድር እንዳይደለች ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ ከእግዝአብሔር የተሰጣት ልዩ ቃል ኪዳን ያላት ሀገር እንደሆነች በድጋሚ ላሳስባችሁ እወዳለሁ፡፡ በቅዱሱ መጽሐፍ ውስጥ ከአርባ አራት ጊዜ በላይ ኢትዮጵያ የሚል ስም ተጽፎ የሚገኝ ሲሆን የባንድራዋ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል፡፡ መዘሙረኛው ዳዊት በምዕ 74፡14 ላይ ሲናገር አንተም የዘንዶን ራሶች ቀጠቀጥህ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው ይልና ምዕ 68፡31 ላይ ስትመለከቱ መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆቹዋን ወደ እግዚአብሔር ታነሳለች ብሎ ከዘጋ በኋላ ት/አሞጽ 9፡7 ላይ ስትመለከቱ የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን በማለት ጥያቀን ለእስራኤል ልጆች ያቀርባል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ልዩ ቃል ኪዳን ያላት ኢትዮጵያ በምናምንቴዎች ሰራ ስትናጥ ውስጤ አዘነ አይኔም አነባ፤ ነገር ግን ከሰማይ አጽናኙ ድምጽ ሲመጣ እንደገና በረታሁ፤ የመጣው የእግዚአብሔር ድምጽ የኢትዮጵያን ድንኳን የሚያስጨንቁትን ከመንግሥት አይን የተሰወሩትን እቀጣለው፤ የገቡበትን እየገባው አስጨንቃቸዋለሁ አለ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ተደብቆና ተሰውሮ ለኢትዮጵያ ወድቀት ሥራን የሚሰሩ ሞትን ሲቀምሱ የኢትዮጵያን ክብር የሚጠባበቁና ለኢትዮጵያ ክብር የሚጸልዩ ከፍታዋን ያያሉ፡፡ የኢትዮጵያ ጉዳይ ወንዝ ሁሉ ቀለም ቢሆን ቅጠል ሁሉ ወረቀት ቢሆን ተጽፎ የማያልቅ ሆነና ወደ ሚቀጥለው ሀሳብ ልግባ፡፡
 ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ ዶ/ር አብይ ልሻገርና ትንሽ ነገር ልናገር የመናገር መብት የሰጠን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ አደራ ተሸክሞ ቀንና ለሊት ተራራ እየወጣ ሸለቆ እየወረደ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በሜድትራንያ ሀይቅ ላይ ብዙ ሰዎችን ጭኖ አውራቂስን እንደሚሰነጥቅ መርከብ ጦርነቱንና ዛቻውን ስድቡንና ማንቁዋሸሹን ሳይፈራ አላማውን ከግብ ለማድረስ ሁኔታዎችን እየሰነጠቀ በመጓዝ ላይ ያለው ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ ሊወቀስ ሳይሆን ሊደነቅ ይገባል ባይ ነኝ፡፡ ድህነት ርሃብና ኋላ ቀርነት አንገት ያስደፋውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሌሎች ኃያልን አገሮች ጋር እኩል ለማድረግ የከፈልከው ዋጋ ከትውልድ ልብ የሚጠፋ አይደለም፡፡
 አልቅሰህ ያሳቅከን ወድቀህ ያነሳኸን፣ ተጨንቀህ ያስደሰትከን፣ ተርበህ ያጠገብከን፣ ወርደህ ያወጣከን፣ ለለውጥ ቆርጠህ የቆመህ መሪ መሆንን በዓለም ሁሉ አስመስክረሃል፡፡
 በፖለትካ ቅራኔ የተጠላለፉ በዘረኝነት መንፈስ የሰከሩ ስራ ፈት ወረኞች በማህበራዊ ሚዲያ ከፍ ዝቅ እያደረጉ የሚንጫጩ የተሸነፈና የወደቁ ስለሆኑ ቦታ አትስጣቸው ትንሳኤ የላቸውምና፣
 ትልቅ ተስፋ ታጥቀህ የሚፈፀም ራዕይ ሰንቀህ እንደ ጥቅምት አበባ ደምቀህ ደስ አለኝ ብቅ ስትል በእግዚአብሔር ተመርጠህ፣
 እውቀትህ ይገርማል ንግግርህ ይፈውሳል እንደ ነብይ ትተነቢያለህ እንደ መምህር ታስተምራለህ እንደ አባት ትመክራለህ ረጅም ዕድሜ ይጨምርልህ፣
 አባት ነህ እንደ አብርሃም ንጉሥ ነህ እንደ ዳዊት ነብይ ነህ እንደ ሙሴ ካህን ነህ እንደ ኢያሱ ጠቢብ ነህ እንደ ሰለሞን ደፋር ነህ እንደ ጳውሎስ ታጋሽ ነህ እንደ ኢዮብ ቆራጥ ነህ እንደ ሂሩት ባለራዕይ ነህ እንደ ዮሴፍ ሳይሰነዝር የሚጥል ጌታ ጠዋትና ማታ ከአንተ ጋር ስለሆነ ያለምከውን ሁሉ ወደ ፍፃሜ ሳታደርስ አትሞትም፡፡
 መስግድ ገብተህ እንደ ሼኪ ቤተመቅደስ ገብተህ እንደ ቄስ ቤተክርስቲያን ገብተህ እንደ መጋቢ ቤተ-መንግሥት ውስጥ ሆነ እንደ ንጉሥ ጥበብህ እንደ አባይ ወንዝ ነው ተግድቦ አያልቅም፡፡
 የሠላም ታጋይ የአንድነት ምስሶ የማለዳ ፀሐይ ዓላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሠራዊት ታስፈራለህ በሕይወትህ ዕድሜህ ሁሉ ማንም አይቋቁምህም እንደ ኢያሱ ዛሬም ጉልበታም ነህ፡፡
 የተጀመረውን አስቀጥለህ ያልተጀመረውን አስጀምረህ በከፍታ ላይ ኢትዮጵያን ለማውጣት ያየኸውን እይታ እጅግ በጣም አደንቃለሁ፡፡
 አንተ የሠራከው ሥራዎች አፍ አላቸው ያወራሉ አይን አላቸው ያያሉ ስነፎች ስለካዱ እኔ አልክድም፣ ኢትዮጵያ ያንተን ክብር ሳታይ አንተም የኢትዮጵያ ክብር ሳታይ ምዕራፍ አይዘጋም፡ እውነቱ ይህ ነው፡፡
 ንጉሥ ለሚጠብቁ ኢትዮጵያዊያን አገልጋይ ሆነ መምጣትህ የመምራት ብቃት የለውም የሚል የስንፍና ንግግር እንዲሰነዝሩ ቢያስችልም አንተ የክርስቶስን ባህር የምትከተል አንደኛና ብቸኛ መሪ መሆንህን አለም ሁሉ መሰክሯል፡፡
 አብይ ለእኔ ልዩ ሰው ነው ልዩነቱ የእግዚአብሔር አብሮነት ነው ጥበቡም ከሰማይ ነው፣ በጥይት የሚመለሰውን በፑሻፕ እየመለሰ ቦንብ ሲወረውሩበት በኢየሱስ ስም እየተከለለ በአጠገቡ ሺህ በቀኙ አሥር ሺህ እየወደቁ እሱ ግን ዛሬም ቆሟል የጌታን ማዳን እየዘመረ፣
 የፍትህ ፀሐይ ለኢትዮጵያ ያበቀልክ መንግሥትህ እንደ ዳዊት መንግሥት ነው፣ እየበረታ ይሄዳል ጉልበትህ እንደ ዋልያ ጉልበት ነው፣ እየጠነከረ ይጨምራል የጥበብህ ጥልቀት ፈልሳፋዎችን ገና ከሩቅ ይጠራል፣ ኃይል እንደታደሰ ንስር ፍጥነቱ ጨምሮ አብይ ሲበር ጠላቶቹ ክንፉ እንደተቆረጠ አሞራ ሰፈር ለሰፈር ሲበታተኑ አየሁ፣
 በጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ መግዛት 100% ያመነ 75% ያመነ 50% ያመነ ምንም ያለመነ ይሰማ በኢትዮጵያና በነገሥታቶቹዋ ታሪክ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ሰው ዶ/ር አብይ ነው፡፡ እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ጉዳት ለመካስ በጓዳ ያሳደኩት የኢትዮጵያ የካሣ ልጄ ነውና ጠላት አይኑ እያዬ ልጄ አብይ ክብሩና ሞገሱ ዝናውና ግርማው ጨምሮ መግዛቱን ይቀጥላል አለ፤
 ኢትዮጵያን ለማንም የማይሰጥ የቁርጥ ቀን ልጅ መሆኑን አውቃችሁ የአብይ ጠላቶችና የኢትዮጵያ ጠላቶች በሙሉ ተስፋ ቆርጣችሁ እጃቹሁን ቶሎ ከኢትዮጵያ ሰብስቡ ዶ/ር አብይም ሆነ መንግሥቱ በቀላሉ የሚወድቅ አይደለም፣ የ27 ዓመታት ታሪክን ገልብጦ በአንድ ዓመት ውስጥ አዲሲቷን ኢትዮጵያ የፈጠረ ከንግግር አልፎ በሥራ ያሳዬ ጀግና መሪያችን ነው ዶ/ር አብይ፣
 እግዚአብሔር ለእኔ ስለ አብይ ሲናገር አብይ የኢትዮጵያ የስኬት ቁልፍ ነውና ሌላ አብይን እስከምተካ ድረስ በሥልጣኑ ይቀጥላል አለ፣
 በአብይ እና በመንግሥቱ ላይ የቀና ጠላት ጆሮ እየሰማ አይኑ እያዬ ለጠ/ዶ/ር አብይ መልዕክት አለኝ 1ኛ ዜና ምዕ 29፡25 ላይ የእግዚአበሔር ቃል ሲናገር እግዚአብሔርም ሰለሞንን በእስራኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገነነው ከእርሱ በፊትም ለነበሩት ለእስራኤል ነገሥታት ያልሆነውን የመንግስት ክብር ሰጠው ፣ ቀጥሎም 2ኛ ዜና 4፡1 ላይ ቅዱሱ መጽሐፍ ሲናገር የዳዊት ልጅ ሰለሞን በመንግሥቱ በረታ አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር እጅግም አገነነው ብሎ እንደተናገረው ሁሉ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ይበረታል ግዛቱ ይሰፋል ገና በዓለም ነገሥታት ጆሮ ሁሉ አገነዋለሁ አለ፡፡ አብይ እየገነነ ሲሄድ አሸባሪዎች እየመነመኑ ይሄዳሉ፣
 አጣልቶ የከበሩ አስታርቆ የነገሰውን ለመጣል ማሰቡ የማይሳካ ትግል ስለሆነ እጃቸውን በጊዜ ቢሰበስቡ ይሻላቸዋል ብዬ እመክራቸኋለሁ፡፡ እግዚአብሔር ዶ/ር አብይን ለመረዳት በደመና ላይ ቆሞ አየሁ፤ አድናቆት አበዛ እንደምትሉኝ ግልጽ ቢሆንም መልካም ሰው በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሁል ጊዜ ከሞቱ በኋላ ስለሚደነቁ ያንን ኬላ ለመስበር ስል ሰዎች በሕይወት እያሉ ማድነቅን ለማስተማርም ጭምር ነው፡፡
 ሰላም ይብዛልህ ኢትዮጵያ በልጆቹዋ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ነብይ እዩ ጩፋ ከ ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች

Show more
Facebook Comments

Up next